በቢሮው ህግን መሰረት በማድረግ ከማዕከል የሚወርዳቸው አቅጣጫዎች በአግባቡ ወደ ተግባር በማሸጋገር የጥር ወር የገቢ እቅድን ማሳካት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የጥር ወር የገቢ አፈፃፀም ለማላቅ በማዕከል እየተካሄደ ያለ የክትትልና ድጋፍ እና የገቢ አፈፃፀምን ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ በመድረኩ ማጠቃለያ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ፤ ከታክስ ኦዲት ፣ ከሀሰተኛ ደረሰኞች ፣ ካልተሰበሰበ ዕዳ ፣ ከገበያዎች ቁጥጥር ፣ ከመኪና አስመጪዎች ፣ ከንግድ ፍቃድ ከማስጠቀስና ደረሰኝ አጠቃቀም ፣ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር እንዲሁም የቅርንጫፍ አመራሩ ስራዎችን እንደቢሮ በሚወርደው አሰራር መሰረት መፈጸም ጋር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በመፈተሸና በማስተካከል የጥር ወር የገቢ እቅድ ማሳካት ይገባል፡፡

በተለየ የሚጠበቀው ገቢ እንደ ቢሮ በወረደው አቅጣጫ መሰረት አሰራሩን ጠብቆ መምጣት እንዳለበት ፣ ገቢን ከማሰደግ አኳያ ካላደረሰኝ ለተገዙ ዕቃዎችና ብሎክን መሰረት በማድረግ የማጥራት ስራ ለሚሰሩ ስራዎችን ከሚመለከታቸው አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ የማድረግ መስራት እንደሚገባ ፣ የመረጃ ስራ አመራር ግንባታ ፕሮጀከት ስራን በአግባቡ መምራትና መፈጸም እንዲሁም በኦዲተሮች ኦዲት የተደረጉ ሰነዶች በድጋሚ በማዕከል ደረጃ ኦዲት እነደሚደረጉ ለንግድ ማህበረሰቡ የማሳወቅ ስራዎችን በአንክሮ መስራት እንደሚገባ ሃላው አስገንዝበዋል ፡፡

በመጨረሻም በቀሪ ቀናት በተቋሙ የታቀደ የ13.3 ቢሊዮን ዕቅድ ለማሳካት የድጋፍና ክትትል ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባና አስፈላጊው ርብርብናቅንጅታዊ አሰራር መሰራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

Related Articles

አዲስ አበባ: ሳርቤት,  የኦሮሚያ ቢሮዎች ጊቢ ዉስጥ

ስልክ ቁጥር : 011-369-15-18/ 011 369- 18-15

ፋክስ ቁጥር: +251-11-371-78-80

ፖ..ቁ: 27475

Email: Oromiarevenues@gmail.com

ፊንፊኔ, ኦሮሚያ

Oromia Revenue Bureau by ORB ICT