ቢሮው በታክስ ኦዲት አፈፃፀም የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና የኦዲት ውሳኔ ጥራትን ማሳደግ ይቻል ዘንድ ከኤች.ኤስ. ቲ አማካሪ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር ከዋና ቢሮና ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተወጣጡ የኦዲት ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።ስልጠናው በኩባንያው ሲኒየር የታክስ ማናጀር በአቶ ማሞ አብዲ እየተሰጠ ሲሆን ዓላማውም የታክስና ኢንተሊጀንስ ኦዲተሮቹ በታክስ ኦዲት አፈፃፀምና ውጤታማነት ፣ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አሰራር እንዲሁም በደንበኞች አገልግሎት ዙሪያ በቂ ክህሎትና ዕውቀትእንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ብለዋል ።
አያይዘውም ከስልጠናው መልስ ባለሙያዎቹ የህግተገዥነትን በማሳደግ በፈቃደኝነት ግብሩን የሚከፍል ማህበረሰብ መፍጠር ፣ ጥራት ያለው የኦዲት ውሳኔና ሪፖርት ማውጣት ፣ ፍትሀዊ የሆነ የታክስ ስርዓት እንዲሰፍን ማስቻል ፣ ሙያው የሚጠይቀውን ስነ ምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲሁም ሙያዊ ብቃታቸውን በማሳደግ በገቢ ዘርፍ የሚታዩ የአልግሎትና የመልካም አስተዳደር ክፍተቶችን በመለየትና በመሙላት የሚጠበቀውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ማስቻል እንደሆነ አስገንዝበዋል ።
ስልጠናው ለ3ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከዋና ቢሮና ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተወጣጡ የታክስ ኦዲትና ኢንቨስትጌሽን ኦዲት ባለሙያዎች እየቸሰጠ ይገኛል ።