ዜና

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየተከናወነ ያለው በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ የ ደረሰኝ ህትመት ያለበትን ሂደት ጎበኙ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየተከናወነ ያለው በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ የ ደረሰኝ ህትመት ያለበትን ሂደት ጎበኙ
ከየካቲት 03 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባዉ ልዩ መለያ ኮድ (QR COD) ደረሰኝ ህትመትን አስመልክቶ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ፣ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አብዱረህማን ኢድ ጣሂር፣ በብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተገኝተዉ ህትመቱ ያለበትን ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
የደረሰኝ አጠቃቀምን ለማሻሻል እየተሰሩ ካሉ ዋነኛ ተግባራት ዉስጥ ደረሰኝን በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ ማድረግ መሆኑ ታምኖ ወደተግባር ተገብቷል፡፡
በዚህም መሰረት የደረሰኝ ህትመቱን በኃላፊነት ወስዶ እየሰራ ያለዉ የብርሃንና ሰላም የህትመት ድርጅት የደረሰኝ ህትመቱ አሁን ያለበትን ሂደት በተመለከተ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ሂደት አስጎብኝቶ ሪፖርትም አቅርቧል፡፡
በሪፖርቱም በርካታ ድርጅቶች ደረሰኝ ለማሳተም ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየመጡ መሆኑንና ሌሎችም ለህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ እንዳሉም ተነስቷል ፡፡
በዚህም አመራሩ ከማተሚያ ድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ልዩ መለያ ኮድ (QR COD) ያለበት ደረሰኝ ህትመት የስራ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን የገመገመ ሲሆን በቀጣይ የደረሰኝ ህትመቱን በሚፈለገዉ ደረጃ ለማከናወን ያግዝ ዘንድ ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ የማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ተወሰነ

ከዚህ ቀደም የደረሰኝ ህትመት ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ብቻ መሆኑ በተገለጸው መሰረት ቁጥራቸው 45,226 የሆኑ ግብር ከፋዮች የህትመት ጥያቄ ማቅረብ መቻላቸውን የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የገቢ ዘርፍ አመራሮች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ገልጸዋል፡፡
ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች የህትመት ጥያቄያቸውን ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች መኖራቸውና ይህን ታሳቢ በማድረግ የህትመት ጥያቄ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ እስከ የካቲት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም በውይይቱ ተወስኗል፡፡
እንደ ሀገር በገቢው ዘርፍ የሚሰተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም በርካታ የሪፎርም ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ በውይይቱ የገለጹ ሲሆን በተለይም የማንዋል ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ስርዓትን በማሻሻል የሚፈለገውን የገቢ ዕድገት ማስመዝገብ ያሰፈልጋል ብለዋል፡፡
ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) የተካተተበት ሚስጥራዊ የደረሰኝ ህትመት ሥርዓትን ወደስራ ማሰገባት የሚያስፈልግ መሆኑን ያስገነዘቡት ሚኒስትሯ እስከ አሁን ባለው አፈፃፀም ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
 

አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኦዲት ወሳኔ ጥራትን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው

ቢሮው በታክስ ኦዲት አፈፃፀም የሚስተዋሉ ክፍተቶችንና የኦዲት ውሳኔ ጥራትን ማሳደግ ይቻል ዘንድ ከኤች.ኤስ. ቲ አማካሪ የግል ኩባንያ ጋር በመተባበር ከዋና ቢሮና ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተወጣጡ የኦዲት ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
ስልጠናው በኩባንያው ሲኒየር የታክስ ማናጀር በአቶ ማሞ አብዲ እየተሰጠ ሲሆን ዓላማውም የታክስና ኢንተሊጀንስ ኦዲተሮቹ በታክስ ኦዲት አፈፃፀምና ውጤታማነት ፣ በአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አሰራር እንዲሁም በደንበኞች አገልግሎት ዙሪያ በቂ ክህሎትና ዕውቀትእንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ብለዋል ።
አያይዘውም ከስልጠናው መልስ ባለሙያዎቹ የህግተገዥነትን በማሳደግ በፈቃደኝነት ግብሩን የሚከፍል ማህበረሰብ መፍጠር ፣ ጥራት ያለው የኦዲት ውሳኔና ሪፖርት ማውጣት ፣ ፍትሀዊ የሆነ የታክስ ስርዓት እንዲሰፍን ማስቻል ፣ ሙያው የሚጠይቀውን ስነ ምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲሁም ሙያዊ ብቃታቸውን በማሳደግ በገቢ ዘርፍ የሚታዩ የአልግሎትና የመልካም አስተዳደር ክፍተቶችን በመለየትና በመሙላት የሚጠበቀውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብ ማስቻል እንደሆነ አስገንዝበዋል ።
ስልጠናው ለ3ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ከዋና ቢሮና ከሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተወጣጡ የታክስ ኦዲትና ኢንቨስትጌሽን ኦዲት ባለሙያዎች እየቸሰጠ ይገኛል ።

አዲስ አበባ: ሳርቤት,  የኦሮሚያ ቢሮዎች ጊቢ ዉስጥ

ስልክ ቁጥር : 011-369-15-18/ 011 369- 18-15

ፋክስ ቁጥር: +251-11-371-78-80

ፖ..ቁ: 27475

Email: Oromiarevenues@gmail.com

ፊንፊኔ, ኦሮሚያ

Oromia Revenue Bureau by ORB ICT