የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየተከናወነ ያለው በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ የ ደረሰኝ ህትመት ያለበትን ሂደት ጎበኙ

የገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየተከናወነ ያለው በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ የ ደረሰኝ ህትመት ያለበትን ሂደት ጎበኙ
ከየካቲት 03 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ተግባር የሚገባዉ ልዩ መለያ ኮድ (QR COD) ደረሰኝ ህትመትን አስመልክቶ የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ፣ የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ፣ የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አብዱረህማን ኢድ ጣሂር፣ በብርሃን እና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ተገኝተዉ ህትመቱ ያለበትን ሂደት ጎብኝተዋል፡፡
የደረሰኝ አጠቃቀምን ለማሻሻል እየተሰሩ ካሉ ዋነኛ ተግባራት ዉስጥ ደረሰኝን በልዩ መለያ ኮድ (QR COD) የተደገፈ ማድረግ መሆኑ ታምኖ ወደተግባር ተገብቷል፡፡
በዚህም መሰረት የደረሰኝ ህትመቱን በኃላፊነት ወስዶ እየሰራ ያለዉ የብርሃንና ሰላም የህትመት ድርጅት የደረሰኝ ህትመቱ አሁን ያለበትን ሂደት በተመለከተ ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ሂደት አስጎብኝቶ ሪፖርትም አቅርቧል፡፡
በሪፖርቱም በርካታ ድርጅቶች ደረሰኝ ለማሳተም ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየመጡ መሆኑንና ሌሎችም ለህትመት ጥያቄ ያላቀረቡ እንዳሉም ተነስቷል ፡፡
በዚህም አመራሩ ከማተሚያ ድርጅቱ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ልዩ መለያ ኮድ (QR COD) ያለበት ደረሰኝ ህትመት የስራ አፈፃፀም በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን የገመገመ ሲሆን በቀጣይ የደረሰኝ ህትመቱን በሚፈለገዉ ደረጃ ለማከናወን ያግዝ ዘንድ ያጋጠሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

Related Articles

አዲስ አበባ: ሳርቤት,  የኦሮሚያ ቢሮዎች ጊቢ ዉስጥ

ስልክ ቁጥር : 011-369-15-18/ 011 369- 18-15

ፋክስ ቁጥር: +251-11-371-78-80

ፖ..ቁ: 27475

Email: Oromiarevenues@gmail.com

ፊንፊኔ, ኦሮሚያ

Oromia Revenue Bureau by ORB ICT